Energize Colorado Gap Fund – Amharic Translation

አሁን ማመልከት ይችላሉ – ማወቅ የሚገባዎን እነሆ

To return to the language resources page, click here.

 

የ”Energize Colorado Gap Fund” (ኢነርጃይዝ ኮሎራዶ የክፍተት መሙያ ፈንድ) በስቴቱ በሞላ የኢኮኖሚው ሞተር ለሆኑት የአነስተኛ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዞች  ከ$31 ሚሊዮን በላይ የአነስተኛ ንግድ ሥራዎች ብድሮችን እና ግራንቶችን ያቀርባል። ከ25 ያነሱ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች ያሏቸው የግል ንግዶች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እስከ $15,000 ግራንት እና $20,000 ብድር በአንድ ላይ እስከ $35,000 ሊደርስ ለሚችል የገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ። ማመልከቻው አሁን ክፍት ነው፤ መረጃዎች በ”Energize Colorado” (በኢነርጃይዝ ኮሎራዶ) መሰጠታቸው ይቀጥላል።  ስለ “Gap Fund” (ክፍተት መሙያ ፈንድ) መረጃዎችን በቀጣይነት ለማግኘት እዚህ ይመዝገቡ።

እስከ ዲሴምበር 2020 እርዳታውን ለመስጠት እንድንችል ማመልከቻዎች እና መረጣዎች በዙር የሚከናወኑ ይሆናል። ሂደቱ መጀመሪያ የመጣ መጀመሪያ ያገኛል አይሆንም፤ እርዳታውን ይበልጥ የሚፈልገው እንዲጠቀምበት ለማስቻል የውድድር ሂደት ይሆናል። ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ይመልከቱ።

ትግበራው በአሁኑ ጊዜ ተዘግቷል ፣ ስለ ጋፕ ፈንድ በ Energize ኮሎራዶ በኩል ስለ ዝመናዎች ይመዝገቡ ፡፡ ይህ የብዙ ዓመት መርሃግብር ነው እና ለማመልከት ብዙ እድሎች ይኖራሉ። ከተፈለገ አሁንም ክፍት መተግበሪያዎን ሊደርሱበት ይችላሉ።

የማመልከቻው የአማርኛ ትርጉም መተግበሪያውን ይድረሱበት

የማመልከቻ ሂደቱ

  • ለማመልከቻው እና ለመረጃዎች ከዚህ በላይ ያሉትን አገናኞችን ይከተሉ።
    • የመስመር-ላይ (online) ማመልከቻው በእንግሊዝኛ ነው። ነገር ግን ማመልከቻውን ለመሙላት የሚረዳዎ የአማርኛ ትርጉም መመሪያ ያገኛሉ።
    • የመስመር-ላይ (online) ማመልከቻውን ለመሙላት መመሪያውን ያውርዱና ይጠቀሙ እባክዎ።
    • የመስመር-ላይ (online) ማመልከቻውን በአማርኛ ወይም በሌላ በመረጡት ቋንቋ ሊሞሉት ይችላሉ።
  • ማመልከቻዎን ከመጀመርዎ በፊት ሠነዶችን ያሰባስቡ እባክዎ። በኮቪድ-19 የሕዝብ ጤና ድንገተኛ ወረርሽኝ ምክንያት ያጋጣሙ የኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚያሳዩ የተለያዩ ሠነዶችን መቀበል እንችላለን። በኮቪድ-19 የደረሰብዎን ጫና የሚያሳዩ ሠነዶችን ያሰባስቡ። ለምሳሌ፦
    • የባንክ ሠነዶች
    • የሽያጭ ደረሰኞች
    • የትርፍና ኪሣራ መግለጫዎች (ስቴትመንቶች)
    • ታክስ ያሳወቁባቸው ሠነዶች
    • የወጭ ደረሰኞች
  • “Energize Colorado” ትርጉምን ጨምሮ ማመልከቻውን ለመሙላት የሚያስችል ምክርና እገዛ ፕሮግራም ይኖረዋል። በመስመር-ላይ (online) የሚገኘውን መረጃ አንብበው አሁንም ጥያቄዎች ካሉዎ የቴክኒካዊ ቡድናችን እርዳታ ይጠይቁ እባክዎ። ቀላል ጥያቄዎችን ለመመለስ ወይም ማመልከቻው በሚለቀቅበት ጊዜ አስቀድመው ሠነዶችን እንዲያዘጋጁ ለማገዝም ዝግጁ ነን። ወደ 1-800-471-0628 (በሳምንት 7 ቀናት ከ 6 a.m. – 6 p.m.) ሊደውሉልን ወይም ወደ  [email protected] ኢሜል ሊልኩልን ይችላሉ።

ብቁ የሚሆነው ማን ነው?

  • አነስተኛ ንግዶች/ኢንተርፕራይዞች – የኮሎራዶ “ሶል ፕሮፕሪያተሮች” እና LLCዎችን፣ S-Corps እና ሌሎች የቢዝነስ ዓይነቶችን ጨምሮ የተመዘገቡ አነስተኛ ንግዶች።
  • ለትርፍ ያልተቋቋሙ – ተልዕኳቸው እና/ወይም ፕሮግራማቸው የአነስተኛ ቢዝነሶች ወይም ቱሪዝም የኢኮኖሚ ልማትን በቀጥታ ለመደገፍ የሆኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የኮሎራዶ ድርጅቶች።
  • ከ25 ሠራተኞች በታች ያላቸው – አመልካቾች ከ25 የሙሉ ጊዜ ሠራተኛዎች (FTE) ያላቸው መሆን አለባቸው። ቀጣሪዎች የጊዜያዊ ሠራተኞን (ሥራ በሚበዛበተ ጊዜ የሚቀጠሩ ሠራተኞችን) አለመቁጠር ይችላሉ።
  • በኮቪድ-19 ጫና ጉዳት የደረሰባቸው – አመልካቾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በቢዝነሳቸው ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ማሳየት መቻል አለባቸው። ቢዝነሱ በኢኮኖሚ ጫና ያለፈበትን ታሪክ እና እንደ ባንክ መግለጫዎች፣ የሽያጭ ደረሰኞች እና የኪሣራ መግለጫዎች ወይም ሌሎች ሠነዶችን ተጠቅሞ የኢኮኖሚ ጫናውን ወይም ጉዳቱን ማሳየት ይቻላል።

ለሚከተሉት ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፦

  • መስፈርቶቹን የሚያሟላ ማንኛውም የኮሎራዶ አነስተኛ ቢዝነስ ለማመልከት ይችላል። ለሚከተሉት አመልካቾች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፦
    • በጥቁሮች፣ በአገር በቀል አሜሪካዊያን፣ ነጭ ባልሆኑ፣ በአርበኞች ወይም በሴቶች የተቋቋሙ ቢዝነሶች
    • ከ50,000 ሕዝብ በታች በሚኖርባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚገኙ ቢዝነሶች
    • በቱሪዝም ዘርፉ ውስጥ ያሉ
    • ካፒታል ፋይናንሲንግ ወይም ሌላ የፌደራል፣ የስቴት ወይም የከተማ ግራንቶችን/ብድሮችን ለማግኘት የማይችሉ

ለተጨማሪ መረጃ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ገጻችን ይጎብኙ።

 

Subscribe to our newsletter and Gap Fund updates here.


First Name
Last Name

Questions about the Gap Fund?  Contact: 1-800-471-0628
(Mon.-Fri. 6 a.m.-8 p.m., Sat.-Sun. 6 a.m.-3 p.m.)
or e-mail
[email protected]

Learn more about the Gap Fund by visiting our Frequently Asked Questions.

Scroll to Top